ስለፈንዱ መቋቋም

የውሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ለከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም ለሰፋፊና መካከለኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል ፋይናንስ ከፌደራል መንግስት ከውጭ አበዳሪና እርዳታ ሰጪ ተቋማትና አገሮች እያፈላለገ የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ ከውሃ ዘርፍ አስተዳደር ፖሊሲና ስትራቴጂ መርሆች አንዱ በሆነው ዋጋን በማስመለሰ መርህ (cost recovery principle ) ላይ በመመስረት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በረጅም ጊዜ እና በአነስተኛ ወለድ የሚከፈል ብድር ለመስጠት ታስቦ በጥር ወር 1994 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 268/1994 የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው ፡፡

ተልዕኮ

የከተሞች የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሽፋን ለማሳደግ እና የመስኖ ልማትን ለማስፋፋት እንዲቻል ከተለያዩ የፋይናንስምንጮች የሚገኘውን ገንዘብ የብድር መስፈርት ለሚያሟሉ የከተሞች ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቶች እና ለመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ማህበራት ብድር መስጠት ብሎም ብድሩን በወቅቱ በመሰብሰብ ለሌሎች ተመሳሳይ የልማት ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል የተዘዋዋሪ ፈንድ ክምችት መፍጠር ነው ፡፡

ራዕይ

በ2017 ዓ.ም ለከተሞች የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ልማት ግንባር ቀደም የፋይናንስ ተቋም መሆን ነው

እሴቶች
 • ቅልጥፍና እና ጥራትን ያገልግሎታችን መለያ ባህሪ ማድረግ
 • ሀብትን በቁጠባ ለተልእኳችን ስኬት ማንዋል
 • ፍትሃዊ የብድር ተጠቃሚነት ማስፋት
 • በጽናት እና በቁጭት ህዝብን ማገልገል
 • ከተግባር ሁሌም መማር
 • ለዉጤታማነት በቡድን መስራት
 • ለሰዉ ሀብት ልማት ትኩረት መስጠት
ተግባር እና ኃላፊነት
 • ለፕሮጀክቶች  ማስፈጸሚያ የሚዉል ፈንድ ከተለያዩ ፋይናንሰሮች የማፈላለግ ተግባር ማከናወን
 • ከተለያዩ ፋይናንሰሮች የተገኘዉ ገንዘብ ወደ ጽ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ እንዲሆን ተገቢዉን ክትትል ማድረግ
 • ብደር ለመፍቀድ የሚያስፈልጉ የጥናት፤የዲዛይንና የበኒእነስ ፕላን ሰነዶች ደረጃቸዉን ጠብቀዉ ተዘጋጅተዉ እንዲቀርቡ ሙያዊ እገዛ መስጠት
 • ለብድር የሚያበቃ ደረጃዉን የጠበቀ ጥናት የሌላቸዉን ፕሮጀክቶች በመለየት ደረጃቸዉን ጠብቀዉ እንዲዘጋጁ ተገቢዉን እገዛና ክትትል ማድረግ
 • የፕሮጀክት አዋጭነት ግምገማ በማካሄድ የግምገማ ዉጤቱን መሰረት ያደረገ ብድር መፍቀድና የብድር ስምምነት መፈራረም
 • የጨረታ ሰነድ፤የጨረታ ግምገማ ዉጤትና የኮንትራት ዉል ሰነዶች ጥራታቸዉን ጠብቀዉ በአግባቡ መዘጋጀታቸዉን በመገምገም ይሁንታ መስጠት
 • ከፕሮጀክቶች አስፈጻሚ አካላት የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎች አግባብነት ያላቸዉ መሆኑን እያረጋገጡ በዉሉ መሰረት ክፍያ መፈጸም
 • በብድር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች በተገቢዉ ጥራትና በወቅቱ ተጠናቀዉ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ሙያዊ እገዛና ክትትል ማድረግ
 • ከፈንዱ ብድር ያገኙ  ተቋማት የአቅም ግንባታ  ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
 • ብድር የወሰዱ ተቋማት ብድራቸዉን የመመለስ አቅማቸዉን በመገምገም አስፈላጊዉን  እገዛ ማድረግ
 • የብድር ገንዘብን በተያዘለት ወቅትና የጊዜ ገደብ ዉስጥ በመሰብሰብ የተሰበሰበዉን ገንዘብ በተዘዋዋሪ ፈንድነት ለሌሎች ተመሳሳይ ዓላማዎች  እንዲዉል ማድረግ
ዜና

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ፡፡

Login with
 
  Login With ማህበራዊ ድህረገፅ በመጠቀም ይግቡ