የውኃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ያስጠናቸው ልዩ ልዩ ሥራዎችን መተግበሪያ ማንዋሎች ግምገማ ዓውደ ጥናት በአዳማ ከተማ ተካሄደ

የውኃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ያስጠናቸው ልዩ ልዩ ሥራዎችን መተግበሪያ ማንዋሎች ግምገማ ዓውደ ጥናት በአዳማ ከተማ ተካሄደ::
አዳማ መጋቢት 28 ቀን 2011 ዓ.ም፤ የውኃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ያስጠናቸው ልዩ ልዩ ሥራዎችን መተግበሪያ ማንዋሎች ግምገማ ዓውደ ጥናት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በዓውደ ጥናቱ ላይ ቀርበው ግምገማ የሚካሄድባቸው ሰነዶች በቁጥር አራት ሲሆኑ ለብድር የሚታጩ የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ብቁነት የሚመዘኑበት ማንዋል፣ የተጨማሪ ወይም አማራጭ ፈንድ ምንጮች ማንዋል፣ የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች አዋጭነት ግምገማ ማንዋል እና የከተሞች መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ግምገማ ማንዋል ናቸው፡፡
ማንዋሎቹን ማስጠናትና ለውይይት ማቅረብ ያስፈለገው ጽ/ቤቱ በዓለም ካለው ተለዋዋጭ ሁኔታ አንጻር በየጊዜው አሠራሩን ለማሻሻል ጥረት የሚያደርግ በመሆኑ እነዚህ ማንዋሎች የማሻሻያ ሥራው አካል በመሆናቸው እንደሆነ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዋና ዋኬ ተናግረዋል፡፡
በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው የውኃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት በሀገሪቱ ለሚገነቡ የመጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች በአነስተኛ ወለድ በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር ፈንድ የሚያቀርብ በአዋጅ የተቋቋመ ጽ/ቤት መሆኑን ጠቅሰው መመሪያዎችን፣ ደንቦችን ማንዋሎችን ማዘጋጀት ከታቀደላቸው በላይ ረጅም ጊዜ የሚፈጁትን፣ የጥራት ደረጃ ጉድለት ያለባቸውን፣ ከፕሮጀክቶቹ ውጤታማ አለመሆን ጋር በተያያዘ የብድር አመላለስ ችግር ያለባቸውንና በየክልሎቹ የሚነሱ የፍትሐዊነት ጥያቄን ለመመለስ የሚያስችሉ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

{{related_content.title}}

{{related_content.lead_paragraph}}

  {{related_content.published_date}}
ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
ዜና

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ፡፡

Login with
 
  Login With ማህበራዊ ድህረገፅ በመጠቀም ይግቡ