ጽ /ቤቱ የአንድ ቀን ዉይይት አካሄደ

ጽ /ቤቱ  የአንድ ቀን ዉይይት አካሄደ

የዉሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት በ One WaSH National (OWNP) Program እየተተገበሩ ካሉ 7 መካከለኛና አነስተኛ ከተሞች ማለትም(ሮቤ፣ሃሳሳ፣ጎቤሳ፣ሲሬ፣ሰንዳፋ-በኬ፣ቦዲቲና በደኖ) የመጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ከየክልሎቹ የዉሃ ቢሮ ሃላፊዎች፣ ከፕሮጀክቶቹ አማካሪዎች  የስራ ተቋራጮች እና ዕቃ አቅራቢዎች ጋር  ዉይይት አደረገ፡፡

 መስከረም 29/2013 ዓ.ም በዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር የስብሰባ አዳራሽ የተደረገዉን  ዉይይት የመሩት ክቡር ዶ/ ር ነጋሽ ዋጌሾ  በዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር የዉሃዉ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታና የዉሃ ልማት ፈንድ የቦርድ ሰብሳቢ ናቸዉ፡፡በዉይይቱ ወቅት የዉሃ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ደ/ር በሻህ ሞገሴ እና አቶ ዋና ዋኬ የዉሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር የተገኙ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በጥልቀት ተገምግሟል፡፡በግምገማዉ ወቅትም አንዳንድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ እየተጠናቀቁ መሆናቸዉ የተገለጸ ሲሆን የተወሰኑት ፕሮጀክቶች ግን በተለያዩ ምክንያቶች እየተጓተቱ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመጨረሻም ለፕሮጀክቶቹ መጓተት አንዳንድ የስራ ተቋራጮች የሚያቀርቧቸዉ ምክንያቶች ተቀባይነት እንደሌላቸዉ ሚ/ር ዴታዉ ገልጸዉ ችግሮቹ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተስተካክለዉ ወደ መስመር የማይገቡ ከሆነ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ በማስጠንቀቅና ቀሪ ስራዎች የሚፈጸሙበትን የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ የዕለቱ ዉይይት ተጠናቋል ፡፡

 

{{related_content.title}}

{{related_content.lead_paragraph}}

  {{related_content.published_date}}
ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
ዜና

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ፡፡

Login with
 
  Login With ማህበራዊ ድህረገፅ በመጠቀም ይግቡ