በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ፡፡

የዉሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ሰራተኞች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ የአንድ ቀን ዉይይት አደረጉ፡፡ በዉይይቱ ወቀቅትም “አገራዊ ሪፎርም ለጠንካራ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ’  እንዲሁም “የህወሐት ኢ- ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴና ፌዴራላዊ ስርዓቱን ለማዳን የተደረጉ ጥረቶች” በሚሉ ሁለት ዐበይት ርዕሶች ስር የተዘጋጁ ጽሁፎች ቀረበዉ ገለጻ ተደርጓል፡፡

በአገራዊ ሪፎርሙ የዉይይት አጀንዳ ስር ከተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ዉስጥ የአገረ መንግስት ፣የብሄረ መንግስትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በርካታ የብሄር ብሄረሰብና ህዝብ ባህል ቋንቋ እምነት የአኗኗር ዘይቤና አመለካከት ባላቸዉ አገሮች ዉስጥ ለሚኖሩ ዜጎች ብቸኛዉ ዋስትና እንደሆነ በክፍል አንድ የዉይይት ፕሮግራም ገለጻ ተደርጓል፡፡

 

በክፍል ሁለት ዉይይት ፕሮግራም ህወሃት የአገራዊ ለዉጡ አካል እንዲሆን መንግስት ሲያደርጋቸዉ የነበሩ ጥረቶች በርካታ እንደነበሩ ሆኖም የህወሃት ጁንታ ቡድን ከመነሻዉ ጀምሮ ሲፈጽማቸዉ የነበረዉ የአፍራሽነት ተልዕኮዎች ሳያንሰዉ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በቅርቡ  የፈጸመዉ የክህደት ተግባር አሳፋሪ እንደሆነ በጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ዋና ዋኬ አማካይነት ሰፋ ያለ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ከዚህ አንጻር የዚህን ጁንታ ቡድን ሴራ በመቀልበስ ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለማዳን መንግስት እየወሰደ ያለዉን ህግ የማስከበር እርምጃ እንደሚደግፉና ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ቃል ገብተዋል፡፡

{{related_content.title}}

{{related_content.lead_paragraph}}

  {{related_content.published_date}}
ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
ዜና

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ፡፡

Login with
 
  Login With ማህበራዊ ድህረገፅ በመጠቀም ይግቡ