“ንጹህ አይምሮ ፅዱ አካባቢ”

ጠቅላይ ሚ/ር ዓቢይ አህመድ “ንጹህ አይምሮ ፅዱ አካባቢ” በሚል መርህ ቃል እሁድ ሚያዝያ 6/2011ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ ኢትዮጵያዉያን በነቂስ ወጥተዉ አካባቢያቸዉን እንዲያጸዱ  ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ  የዉሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ሰራተኞች ሚያዚያ 4/2011ዓ.ም  በግቢያቸዉ እና በመግቢያ በር አካባቢ ከፍተኛ የጽዳት ስራ አካናዉነዋል፡፡ከጧቱ 3፡30 ጀምሮ  እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ በተከናወነዉ የጽዳት ስራ ላይ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኛ የተሳተፈ ሲሆን በግቢዉ ዉስጥ ለረዥም ጊዜ ተጠራቅመዉ የነበሩ የቆሻሻ ክምሮች አላስፈላጊ አረሞችና የወዳደቁ ማቴሪያሎች ጭምር እንዲወገዱና እንዲጸዱ ተደርገዋል፡፡

የጽዳት ስራዉ በተጠናቀቀበት ወቅት የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዋና ዋኬ በጽዳት ስራዉ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ በማመስገን የጽዳት ዘመቻዉ ለአንዴ ብቻ ሳይሆን በየወሩ መለመድ እንዳለበት ካስገነዘቡ በኃላ ኢትዮጵያ ካሏት ሃብቶች ዉስጥ የሰዉ ጉልበት አንዱና ዋነኛዉ እንደመሆኑ በዕለቱ የታየዉ ተነሳሽነትና በአጭር ጊዜ ዉስጥ የተከናወነዉ ስራ በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች እንደ ቋሚ ባህል ቢለመድ ለወደፊቱ የአገሪቱ ዕድገትና ብልጽግና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም ዋና ዳይሬክተሩ ሲገልጹ ይህ ዘመቻ ጣምራ ግቦች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው በአገራችን እያቆጠቆጠ የመጣውን ቂም&ጥላቻና ዘረኝነት ማስወገድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በምንኖርባቸው አካባቢዎች ለጤናና ለአካባቢ ውበት ጠንቅ የሆኑትን ቆሻሻዎች ማስወገድ የዚሁ ዘመቻ ግቦች መሆናቸዉን በማንሳት የዚህ አይነቱ ልምድ በመኖሪያ ቤታችንም ሆነ በሰፈራችን ተጠናክሮ ቢቀጥል ቆሻሸን ወደ ሀብትነት መቀየር ከመቻላችንም በላይ በቋሚነት ፅዱ አካባቢ፤ጽዱ አገርና ጽዱ አይምሮ ሊኖረን እንደሚችል አብራርተዋል፡፡

የውኃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ያስጠናቸው ልዩ ልዩ ሥራዎችን መተግበሪያ ማንዋሎች ግምገማ ዓውደ ጥናት በአዳማ ከተማ ተካሄደ

የውኃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ያስጠናቸው ልዩ ልዩ ሥራዎችን መተግበሪያ ማንዋሎች ግምገማ ዓውደ ጥናት በአዳማ ከተማ ተካሄደ:: አዳማ መጋቢት 28 ቀን...

ዜና

“ንጹህ አይምሮ ፅዱ አካባቢ”

ጠቅላይ ሚ/ር ዓቢይ አህመድ “ንጹህ አይምሮ ፅዱ አካባቢ” በሚል መርህ ቃል እሁድ ሚያዝያ 6/2011ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ ኢትዮጵያዉያን በነቂስ ወጥተዉ አካባቢያቸዉን...

Login with
 
  Login With ማህበራዊ ድህረገፅ በመጠቀም ይግቡ