የብድር አሰጣጥ

የውሀ ልማት ፈንድ የብድር አሰጣጥ መመሪያ፣

 

የውሀ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ህጋዊ ሰውነት ላላቸው በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት አቅርቦት ለተሰማሩ ተቋማት እንዲሁም በመስኖ ልማት ስራ ላይ ለተሰማሩ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ማህበራት ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የረጅም ጊዜ ብድር ለመስጠት የተቋቋመ መንግስታዊ ድርጅት ነው፡፡ በመሆኑም ከፈንዱ የብድር አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ያሉትን ዋና ዋና ጉዳዮች ማለትም፣ ስለ ብድሩ አይነት፤ ተበዳሪዎች ማሟላት ስለሚገባቸው መስፈርት፤ ስለፕሮጀክት አዋጭነት ግምገማ፤ ስለብድር ማጽደቅ፤ ስለብድሩ አሰጣጥ ደንቦችና ሁኔታዎች / Loan Terms and Conditions/ ፤ ስለ ግዢና ክፍያ አፈጻጸም ሂደት ፤ ስለብድር ፈንድ አመዳደብና ዝውውር ፤ስለወጪ መጋራት፤ ስለሂሳብና ተያያዥ ምዝገባዎች …ወ.ዘ.ተ የሚመለከቱ ጉዳዮችን የሚይዝና አቅጣጫ አመላካች የሆነ መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ  በውሀ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ 268/94 አንቀጽ 7 ንኡስ አንቀጽ 2 እና አንቀጽ 14 ንኡስ አንቀጽ 4 በሚደነግገው መሠረት የብድር አሰጣጥ መመሪያ ቁ.1/2009 በቦርዱ ጸድቆ በሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

ይህ የብድር አሰጣጥ መመሪያ ጽ/ቤቱ የሚያወጣውን የብድር መመዘኛ መስፈርቶች እስካሟሉ ድረስ በሀገሪቱ የሚገኙ የክልል ከተሞችና የአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደሮችን በፍትሀዊነትና እኩል ተጠቃሚነት  እንዲያገለግል ሆኖ የተዘጋጀ መመሪያ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የብድር አሰጣጥ ማዕቀፈ ወይም መመሪያው ለውሀ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ውሳኔ ሰጪዎችና በስራው ላይ ለተሰማሩ ፈጻሚ ባለሙያዎች ጠቃሚ የስራ መመሪያ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡

ለበለጠ ግንዛቤ የብድር አሰጣጥ መመሪያውን ይመልከቱ

ዜና

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት ተደረገ፡፡

Login with
 
  Login With ማህበራዊ ድህረገፅ በመጠቀም ይግቡ